በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤይሩት ጎተራ ተናደ


በቤይሩት ጎተራ ተናደ
በቤይሩት ጎተራ ተናደ

ከሁለት ዓመት በፊት ቤይሩት ወደብ ላይ በደረሰው ከባድ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰበት ጎተራ ሌላ ክፍል ዛሬ ጠዋት ተንዶ አካባቢውን የአቧራ ደመና አልብሷል።

ከረጅም ግዜ በፊት ሰዎች ከአካባቢው እንዲለቅቁ በመደረጉ በህይወትና በአካል ላይ አደጋ አለመደረሱ ተገልጿል።

በወደቡ ላይ ያለፈው ፍንዳታ ሲደርስ የ48 ሜትር ከፍታ ያለው ጎተራ የፍንዳታውን ኃይል መቋቋም ብቻ ሳይሆን የከተማዪቱን ምዕራባዊ ክፍል ከአደጋ መሸፈኑ ተዘግቧል።

ወደቡ ላይ ያላግባብ ተከማችቶ ነበር የተባለ አሞኒየም ናይትሬት የዛሬ ሁለት ዓመት ያደረሰውና ለ215 ሰው ሞትና ከ ስድስት ሺህ በላይ ጉዳት ምክንያት የሆነ ፍንዳታ በታሪክ ‘ኒኩሌር ያልሆነ ከባዱ ፍንዳታ’ ተብሎ ተመዝግቧል።

መንግሥት የጎተራው ደቡባዊ ክፍል እንደቆመ የሚቆይበትን መላ እየፈለገ መሆኑን የሃገሪቱ ባላደራ መንግሥት ሚኒስትር ያሲር ያሲን ለሊባኖስ ቴሌቪዝን ተናግረዋል። በወደቡ አካባቢ ያሉ ሰዎችም የፊት ጭንብል እንዲጠቀሙ መክረዋል።

መንግሥት ባለፈው ሚያዝያ ጎተራውን ለማፍረስ ሞክሮ ከፍንዳታው ሰለባ ቤተሰቦችና ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች ‘ፍንዳታውን በተመለከተ ለሚደረገው ህጋዊ ምርመራ የሚያስፈልግ መረጃ ሊኖረው ይችላል’ በሚል ተቃውሞ ስለገጠመው ማፍረስ እንዳልቻለ ይናገራል። ለተሰዉት ሰዎች መታሰቢያ እንዲሆን ባለበት ቆሞ መቅረት ይገባዋል ሲሉ የሰለባው ቤተሰቦች ጠይቀው ነበር።

50 ዓመት የሆነው የዚህ ጎተራ ሌላው ቀሪ ክፍል ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ በውስጡ የያዘው እህል በመፍላላቱ እና በእሳት በመያያዙ እያጋደለ በመምጣት ላይ መሆኑን የአሶሲዬትድ ፕረስ ዘገባ ጨምሮ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG