በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በጋዛ ዘመቻዋን ስታሰፋ በቤይሩት ከባድ የአየር ድብደባ ፈጽማለች


በእስራኤል የአየር ድብደባ በዳሂህ ፣ ቤይሩት ፣ ሊባኖስ የቃጠሎ ጭስ ይታያል፤ እአአ ኅዳር 7/2024
በእስራኤል የአየር ድብደባ በዳሂህ ፣ ቤይሩት ፣ ሊባኖስ የቃጠሎ ጭስ ይታያል፤ እአአ ኅዳር 7/2024

በሊባኖስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኘውን አካባቢ ጨምሮ በደቡባዊ ቤይሩት አካባቢዎች ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ከፍተኛ የአየር ድብደባዎች ተፈጽመዋል፡፡

የእስራኤል ጦር በአካባቢው የሂዝቦላህን መገልገያዎች መኖራቸውን በመጥቀስ ሰዎች አካባቢውን እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ተጨማሪ ዝርዝሮችን አልሰጠም፡፡

በተጨማሪም የእስራኤል ጦር፣ ከጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ ከባድ የቦምብ ድብደባ የተፈፀመባትንና የሀማስ ታጣቂዎች መልሰው እየተቧደኑባት ነው ያላትን ቤት ላሂያ ከተማን በማካተት በሰሜናዊ ጋዛ ለወራት የቆየውን የምድር ዘመቻ ማስፋፋቱን አስታውቋል፡፡

በእነዚህ አካባቢዎች የተፈጸሙ ከባድ የቦምብ ጥቃቶች ከፍተኛ ጉዳት እና የጅምላ መፈናቀል አድርሰዋል፡፡

የሂዝቦላህ መሪ ናኢም ካሴም፣ የቀድሞ የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ፣ በቤይሩት ከተገደሉበት ጊዜ አንስቶ ለ40 ቀናት የቆየውን የሃዘን ጊዜ አስመልከተው ትላንት ረቡዕ ባሰሙት ንግግር “የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ለተኩስ አቁም ድርድር ክፍት የሚሆነው አንዴ ነው ፣ ‘ጠላት ጥቃቱን ካቆመ’ ብቻ” ብለዋል።

ሄዝቦላህ በጋዛ ሰርጥ ከሚገኘው የሃማስ ታጣቂ ቡድን ጋር በመተባበር እኤአ ከጥቅምት 8፣ 2023 ጀምሮ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ሲተኩስ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ፣ “በሊባኖስ ከ3,000 በላይ ሰዎች ሲገደሉ 13,600 የሚያህሉ ቆስለዋል” ሲል የሌባኖስ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዘግቧል።

የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት የተቀሰቀሰው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7፣ 2023 የፍልስጤም ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ዘልቀው በመግባት አብዛኞቹ ሲቪሎች የሆኑትን 1,200 ያህል ሰዎችን ከገደሉ እና ሌሎችን 250 ከጠለፉ በኋላ ነው።

እስራኤል በጋዛ በወሰደችው ወታደራዊ ምላሽ ከ43,000 በላይ ሰዎችን መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

በሰላማዊ ሰዎች እና በታጋዮች መካከል ያለውን ልዩነት ባይገልጹም ከተገደሉት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG