በአማራ ክልል በግጭት ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ ተካሂደ፡፡
ሰልፈኞቹ በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የቱሪዝም እንቅስቃሴው ተስተጓጉሏል፤ የከፋ ድህነት እየተስተዋለ ነው ብለዋል፡፡
ሰልፉ በመንግሥት ትእዛዝና አስገዳጅነት እንጅ በሕዝብ ፍላጎት የተዘጋጀ አይደለም ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩም አሉ፡፡
የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ሰልፉን ከአጎራባች ወረዳዎች ጋራ በመተባበር ማዘጋጀቱን አስታውሶ በፈቃደኘነት እንጅ በአስገዳጅ ትእዛዝ የተሳተፈ የለም ሲሉ ትችቱን አስተባብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም