ኢትዮጵያ፣ የቤት ሠራተኞችንና የፍልሰተኛ ሠራተኞችን መብቶች ለማስከበር፣ እንዲሁም በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የወጡ አራት ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እንድታጸድቅ፣ የአገሪቱ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፈደሬሽን ጥሪ አቀረበ።
የኮንፈደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ ሀገራት በቤት ሠራተኝነት ተቀጥረው በሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ ልዩ ልዩ በደሎች እንደሚፈጸሙ ገልጸው፣ መብቶቻቸውን ለማስከበር የሕግ ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የቤት ሠራተኞችና ከስደት ተመላሾች በበኩላቸው፣ በአሠሪዎቻቸው የመብቶች ጥሰት እንደሚፈጸምባቸው ገልጸው፣ መንግሥት እና ኅብረተሰቡ ችግሩን ለመቅረፍ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም