በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰራተኞች ቀን


ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ የሰራተኞች ቀን በዓልን አክብራ ውላለች።

የሰራተኞች ቀን በዓል ለሰራተኞችና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ክብር የሚሰጥበት ዕለት ነው።

እአአ በ 1880 ዎቹ ዓመታት የአሜሪካ ሰራተኞች በቀን ለ 12 ሰዓታት፣ በሳምንት ደግሞ ለስድስት ቀናት በትንሽ ደምወዝ ይሠሩ ነበር። የአምስት ዓመት ዕድሜ ህጻናት ሳይቀሩ አስከፊ ይዘት ባላቸው ፋብሪካዎች ለመስራት ይገደዱ ነበር። የጤና ጥበቃ ጥቅም ማግኘት የሚባል ነገርማ ተሰምቶም አያውቅም ነብር። ስለሆነም ለሰራተኞቹ ልፋት ዕውቅና እንዲሰጥ ግፊት ይደረግ እንደነበር ታውቋል።

የሀገሪቱ ክፍለ-ግዛቶች ለሰረቶኞቹ ክብር የሚሰጥበት ቀን ለመመደብ አንድ በአንድ ህግ ማውጣት ጀመሩ።

እአአ ሰኔ 28 1884 የሀገሪቱ ምክር ቤት በየዓመቱ የመስከረም ወር የመጀመርያው ሰኞ የሰራተኞች ቀን እንዲሆን ወሰነ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG