በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ትረምፕ ሩሲያ ወደ ቡድን ሰባት እንድትመለስ ላቀረቡት ጥያቄ፣ ክሬምሊን ቡድኑ ጠቀሜታውን አጥቷል ስትል ምላሽ ሰጠች

ትረምፕ ሩሲያ ወደ ቡድን ሰባት እንድትመለስ ላቀረቡት ጥያቄ፣ ክሬምሊን ቡድኑ ጠቀሜታውን አጥቷል ስትል ምላሽ ሰጠች


ሩሲያ ወደ ቡድን ሰባት ሀገራት አባልነት
ሩሲያ ወደ ቡድን ሰባት ሀገራት አባልነት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሩሲያ ወደ ቡድን ሰባት ሀገራት አባልነት እንድትመለስ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ክሬምሊን፣ የቡድን ሰባት ከዚህ በኋላ በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን ሀገራት እንደማይወክል አስታውቃለች።

ትረምፕ ትላንት ሐሙስ "ቢመለሱ ደስ ይለኛል። እነሱን ከቡድኑ ማስወጣት ስህተት ነበር ብዬ አምናለሁ። ሩሲያን የመውደድ እና ያለመውደድ ጥያቄ አይደለም። ይሄ ቡድን ስምንት ነበር።" ብለዋል።

ሩሲያ ቡድን ስምንት ተብሎ ይጠራ የነበረው የዓለማችን ባለጸጋና ኃያላን ሀጋራት ማኅበር አባል የነበረች ሲሆን፣ እ.አ.አ በ2014 ሞስኮ የዩክሬን አካል የነበረውን ክሬሚያ ቀጠና ወደ ግዛቷ መጠቅለሏን ተከትሎ ከቡድኑ እንድትወጣ ተደርጋለች።

የትረምፕን ንግግር ተከትሎ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በሰጡት አስተተያየት "አሁን ቡድን ሰባት ተብሎ የሚጠራው ቡድን ጠቀሜታውን አጥቷል። ከእድገት አንፃር በተለያዩ መመዘኛዎች መሪ ያልሆኑ ሀገራትን የያዘ ስብስብ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የዕድገት ማዕከል ወደሌሎች የዓለም ቀጠናዎች ተሻግሯል" ያሉት ቃል አቀባዩ፣ ይልቁንም "ቡድን 20 በተሰኘው ማዕቀፍ ውስጥ ገንቢ ሥራችንን በተሻለ ሁኔታ የመቀጠል ፍላጎት አለን። ቡድን 20 የዓለምን ኢኮኖሚ የተሻለ ያንፀባርቃል" ሲሉ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG