በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲንና ትረምፕ ተገናኝተው የመነጋገር ሥምምነት እንዳለ የሩስያ ባለስልጣኖች ጠቆሙ

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲንና የዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ዶናልድ ትረምፕ በአንድ፣ ሶስተኝ ሀገር ተገናኝተው የመነጋገር ሥምምነት እንዳለ የሩስያ ባለስልጣኖች ጠቁመዋል።

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲንና የዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ዶናልድ ትረምፕ በአንድ፣ ሶስተኝ ሀገር ተገናኝተው የመነጋገር ሥምምነት እንዳለ የሩስያ ባለስልጣኖች ጠቁመዋል።

ስለጉብኝቱ ዛሬ ይፋ የተደረገው የዩናይትስድ ስቴትስ ብሄራዊ የጸጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን ከፑቲንና ከሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለልስጣኖች ጋር ለመነጋገር ሞስኮ በሚገኙበት ወቅት ነው። የክረምሊን የውጭ ፖሊሲ ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ስለትረምፕና ፑቲን ተገንኝቶ መነጋገር ጉዳይ ነገ ሀሙስ በዝርዝር ይገለፃል ብለዋል።

ትረምፕ እአአ በመጪው ሀምሌ 11 እና 12 ቀናት በኔቶ /በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት/ ጉባዔ ከተሳተፉና ብሪታንያን ከጎበኙ በኋላ ቪየና ወይም ሄሲንኪ ከሩስያው መሪ ጋር ሊገናኙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG