በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮረም እና ኦፍላ ወረዳ ነዋሪዎች ሰብአዊ መብታችን በትግራይ ታጣቂዎች “እየተጣሰ ነው” አሉ


የኮረም እና ኦፍላ ወረዳ ነዋሪዎች ሰብአዊ መብታችን በትግራይ ታጣቂዎች “እየተጣሰ ነው” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:37 0:00

የኮረም እና ኦፍላ ወረዳ ነዋሪዎች ሰብአዊ መብታችን በትግራይ ታጣቂዎች “እየተጣሰ ነው” አሉ

የትግራይ ታጣቂዎች፣ በቅርቡ በያዟቸው የኮረም ከተማ እና የኦፍላ ወረዳ፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን እየፈጸሙ እንደኾነ የከሰሱ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች፣ ጥሰቱ ደብዛን እስከማጥፋትና ድብደባ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

የኮረም ከተማ አስተዳደርም፣ በነዋሪዎቹ የቀረበው ክስ “ትክክለኛ ነው፤” ሲል አረጋግጧል፡፡

የከተማው ከንቲባ ብርሃኑ ኀይሉ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ፣ አራት ሰዎች ታፍነው የደረሱበት አለመታወቁንና ከሰባት የማያንሱ ደግሞ በተፈጸመባቸው ድብደባ መጎዳታቸውን አስረድተዋል፡፡

የደቡብ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ ግን፣ ክሱ “ከእውነት የራቀ እና መሠረተ ቢስ ነው፤” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ በአንጻሩ፣ ሰብአዊ ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ፣ የትግራይ ታጣቂዎች ከሚመለከታቸው የፌደራል አካላት ጋራ በመተባበር እየሠሩ መኾናቸውን፣ ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ ፓርቲ፣ በወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ፣ የራያ ወረዳዎችንና የአላማጣ ከተማ አካባቢዎችን በወረራ ተቆጣጥረዋል ያላቸውን የህወሓት ታጣቂዎች፥ በግድያ፣ በማፈናቀልና በዘረፋ ድርጊቶች ወንጅሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG