በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ኑክሌር ተሸካሚ የባሕር ውስጥ ድሮን መሞከሯን አስታውቀች


ፎቶ ፋይል፦ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን
ፎቶ ፋይል፦ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን

ሰሜን ኮሪያ በባሕር ውስጥ ተጓዥና ኑክሌር ተሸካሚ የሆነ ድሮን መሞከሯን ዛሬ አስታውቃለች፡፡ ሙከራው አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን በጋር ለሚያደርጉት የባሕር ላይ ልምምድ የተሰጠ ምላሽ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም፣ ሙከራው የተደረገው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን አገራቸው ለረጅም ግዜ ይዛ የቆየውችውንና፣ ከደቡብ ኮርያ ጋር በሰላም እንደገና መዋሃድ እንደምትሻ የሚገልጸውን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ የሚሽር እና በምትኩም ደቡብ ኮሪያን እንደ ቀንደኛ የውጪ ጠላት በሚቆጥር አንቀጽ እንደሚተካ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ነው።

ሰሜን ኮሪያ እንዳለችው፣ የባሕር ውስጥ ድሮኑ ባለፈው ዓመትም ተሞክሮ የነበረ ሲሆን፣ የጠላትን መርከቦች እና ወደቦች ለማጥቃት ታስቦ የተሠራ ነው። የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ኃይል በበኩሉ፣ ድሮኑ ያለውን ብቃት በተመለከተ ሰሜን ኮሪያ አጋና አቅርባለች ብሏል።

በኮሪያ ባሕረ ገብ መሬት አካባቢ ያለው ውጥረት ከመቼውም ግዜ በላይ ማየሉ ታውቋል። ሰሜን ኮሪያ የመሣሪያ ሙከራዋን በማጧጧፍ እና የኑክሌር ዛቻ በማድረግ ላይ ስትሆን፣ በምላሹ ደግሞ አሜሪካና በእስያ የሚገኙ አጋሮቿ የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG