ጃፓን ውስጥ በአወዛጋቢው የያሱኩኒ (Yasukuni) መንፈሳዊ ስፍራ በሚገኝ የሕዝብ መጸዳጃ ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ የተጠረጠረ አንድ ደቡብ ኰሪያዊ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ።
በፖሊስ መግለጫ መሠረት የ27 ዓመቱ ዢኦን ቻንግ ሃን (Jeon Chang-han) ዛሬ ሮብ ከደቡብ ኰሪያ ቶክዮ እንደገባ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። የእስካሁኑ ክሱ፣ ቤተ-መቅደሱ ውስጥ ህጋዊ ባልሆነ ምክንያት መግባቱ ነው ተብሏል።
መርማሪዎች ባገኙት መረጃ መሠረት፣ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በቤተ-መቅደሱ የደኅንነት ጥበቃ ካሜራ አማካኝነት፣ እአአ ከኅዳር 23«ኡ» ፍንዳታ ቀደም ብሎ ነው።
በስፍራው ከአንድ መቶ ጎብኚዎች በላይ የነበሩ ሲሆን በዚያ ፍንዳታ ግን አንድም የተጎዳ ሰው እንዳልነበረ ተገልጧል።
ተጠርጣሪው ዢኦን (Jeon) ቶክዮ የገባው ከፍንዳታው ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ሲሆን፣ ወደ ደቡብ ኰሪያ የተመለሰው