በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ንጉሥ ቻርለስ ኬንያን በመጎብኘት በቅኝ ዘመን ለደረሰው በደል ተጸጸቱ


የእንግሊዙ ንጉሥ ቻርለስ ሣልሳዊ፣ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ
የእንግሊዙ ንጉሥ ቻርለስ ሣልሳዊ፣ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ

የእንግሊዙ ንጉሥ ቻርለስ ሣልሳዊ በዓለም ጦርነቶች ከእንግሊዝ ጋር ተባብረው የተዋጉትን የኬንያ ወታደሮች ለማክበር ዛሬ ረቡዕ በመካነ መቃብራቸው ላይ ተገኝተው የክብር አበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

ይህ የሆነው የብሪታኒያ ንጉሥ በቅኝ ግዛት ዘመን ለደረሰው ሁከትና ብጥብጥ የተሰማቸውን “ጥልቅ ሀዘንና ጸጸት” ከገለጹ አንድ ቀን በኋላ ነው፡፡

ንጉሥ ቻርለስ በቅኝ ግዛት ለተፈጸመው በደል የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ቢገልጹም አብዛኞቹ ኬንያውያን እንደሚፈልጉት ይቅርታ አልጠየቁም፡፡

የኬንያ ጉብኘት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና ያለፉትን ስህተቶች ሁሉ በግልጽ ለመፍታት ያለመ መሆኑን በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በተዘጋጀው ብሄራዊ የራት ግብዣ ላይ ንጉሥ ቻርለስ ተናግረዋል፡፡

ንጉሡ ከንግሥት ካሚላ ጋር በመሆን ከንግሥናቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊያዜያቸው በሆነው ጉብኝት ኬንያ የገቡት ባለፈው ሰኞ ነው፡፡

የንጉሡ ጉብኝት ኬንያ 60ኛውን የነጻት በዓል ባከበረችበት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG