በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ አቅራቢያ የጤና ባለሞያዎች ተገድለው ተገኙ


ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅራቢያ በምትገኝ አንዲት መንደር ሰባት የጤና ሠራተኞችና አንድ ሌላ ሲቪል ተገድለው ተገኙ። ድርጊቱ የአካባዊው ነዋሪዎችን፣ ባለሥልጣናት እና አዛውንቶችን አስደንግጧል።

የአካባቢው የሃገር ሽማግሌ ለቪኦኤ የሶማልኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ ሰባቱ ወጣት የጤና ሠራተኞችና የአንድ መደብር ባለቤት የሆኑ ነዋሪዎች ትናንት የሶማሊያ ጦር ሠራዊት መለዩ ልብስ በለበሱ ሰዎች ተጠልፈው ዛሬ አስከሬናቸው ተገኝቷል ብለዋል።

የጥቃቱ ኃላፊ ማን እንደሆነ ባይታወቅም የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሶማሊያ ወታደሮች ናቸው ማክሰኞ ዕለት ዘጠኝ ወታደሮች መንገድ ላይ በተቀበረ ፈንጂ ሰለተገደሉ ለመበቀል ያደረጉት ነው ብለዋል። የወረዳዋ ኮሚሽነር ድርጊቱን አስተባብለው፤ ግድያውን የፈጸመው አልሸባብ ነው ብለዋል። ሰባቱ የጤና ሠራተኞች፣ ዘምዘም ለተባለ የጤና በጎ አድራጎት ድርጅት የሚሠሩ እንደነበሩ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG