ዋሺንግተን ዲሲ- አዲስ አበባ —
ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ላይ ሰሞኑን በተካሄደው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውኃና የመስኖ ሚኒስትሮች አራተኛ ዙር የምክክር ስብሰባ ላይ ግብፃዊያኑ የቀድሞ አቋማቸውን አስተካክለው በመምጣታቸው ስምምነት ላይ ለመድረስ ተችሏል ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ የውኃ፣ የኢነርጂና የመስኖ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
የሚኒስቴሩ የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሙሉውን ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡