በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሦርያና በዮርዳኖስ መካከል ያለ መተላለፍያ ከሦስት ዓመታት በኋላ ተከፈተ


በሦርያና በዮርዳኖስ መካከል ያለ ወሳኝ መተላለፍያ ድንበር በሦስት ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ዛሬ ተከፍቷል።

በሦርያና በዮርዳኖስ መካከል ያለ ወሳኝ መተላለፍያ ድንበር በሦስት ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ዛሬ ተከፍቷል።

የናሲብ ድንበር መከፈት ሊባኖስንም ጨምሮ በክልሉ ላለው የየብስ የንግድ ልውውጥ አስፋላጊ ነው። የሦርያውን ፕሬዚዳንት ባሻር አል-አሳድን የሚቃወሙ አማፅያን ከሦስት ዓመታት በፊት መተላለፍያውን ድንባር ተቆጣጥረው ነበር። ይሁንና የመንግሥት ኃይሎች ባለፈው ሐምሌ ወር አስመለሱት።

ለሰባት ዓመታት በዘለቀው ውጊያ ምክንያት ተዘግቶ የነበረ በሦርያና እስራኤል በምትቆጣጠረው የጎላን ኮረብታዎች መካከል ያለው መተላለፍያ ድንበርም ዛሬ ተከፍቷል።

ኳነተረ የተባለው መተላለፍያ ድንበር ለአራት ዓመታት ያህል ነበር ተዘግቶ የቆየው። ብዙውን ጊዜ የሚጠቀሙበት እአአ በ 1974 በሶርያና በእስራኤል መካከል የተፈረመውን የሰላም ሥምምነት የሚጠብቁ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ሰላም ጠባቂዎች ናቸው።

የመተላለፍያ ድንበሮች መከፈት የአሳድ መንግሥት ከሰባት ዓመታት በፊት በተጀመረው ውጊያ በአማጽያን ተይዘው የነበሩትን ግዛቶች ለማስመለስ በሚያደርገው ጥረት አዎንታዊ እርምጃ ነው ተብልዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG