በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬርያ ኢብራሂም እጃቸውን ሰጡ


የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈጉባዔ የነበሩት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም
የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈጉባዔ የነበሩት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም

የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈጉባዔ የነበሩት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም መቀሌ ውስጥ እጃቸውን ለመከላከያ ኃይሉ መስጠታቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።

ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከዘጠኙ የህወሓት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዷ መሆናቸውን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት የትዊተር ገፅ ላይ የወጣ የመረጃ ማጣሪያው ፅሁፍ ይጠቁማል።

ወ/ሮ ኬርያ በቅርቡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለቅቀው የፓርቲያቸውን አመራር መቀላቀላቸውንም የመረጃ ማጣሪያው አስታውሷል።

XS
SM
MD
LG