በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመን የተኩስ አቁም ስምምነት ሊጀመር ነው


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ

በየመን ሁሉም ባለድርሻ የበኩሉን ከተወጣ የተኩስ አቁም ስምምነቱ የፊታችን ሐሙስ ሊጀመር ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ተናገሩ።

የየመን ታጣቂ ሁቱዎች እንቅስቃሴና በሣዑዲ የሚመራው ወታደራዊ ህብረት ሀገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው ሁከት መፍትሄ ለማግኘት ተስማምተዋል።

ውጥናቸውም እስከ 2016 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ አዲስ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለመመሥረት ነው።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ያቀረቡትን ሃሳብ መሠረት ያደረገው የኦማንየሠላም ዕቅድ ሁቲዎች ከተቆጣጠሯቸው በርካታ ትላልቅ ከተሞች ወጥተው በለውጡ የየመኑ ፕሬዘዳንት አብዱ ራቡ ማንሶር ሃይዲ ሥልጣን ብዙም ከፋፋይ አይሆኑም ለሚባሉት ምክትላቸው እንዲያስረክቡ ይጠይቃል።

XS
SM
MD
LG