ዋሺንግተን ዲሲ —
ሦስት የኬንያ ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የተቃዋሚውን የራይላ ኦዲንጋን የይስሙላ ቃለ-መኃላ በማስተለፋቸው፣ መንግሥት አየር ላይ እንዳይውሉ ያስተላለፈውን ዕገዳ እንዲያነሳ፣ የኬንያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
በዚህ፣ የፕሬዚደንት ኡሑሩ ኬንያታን መመረጥ ለመቃወም በተካሄደው የቀልድ ሥነ ሥርዓት ላይ ግን፣ በአሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች መገኘታቸው ታውቋል። ኦዲንጋ ይህን የፕሬዚዳንት ኡሑሩን ምርጫ፣ “የተጭበረበረ ነው” ነው የሚሉት።
መንግሥት፣ ለማክሰኞው የይስሙላ ቃለ መኃላ ሥነ ሥርዓት በሰጠው መልስ፣ የተቃዋሚው እንቅስቃሴ ሕገወጥና ድርጅቱም ወንጀለኛ መሆኑን አመልክቶ፣ ሥነሥርዓቱን የዘገቡ ጣቢያዎችም እንዳያስተላልፉ አዟል።
ሆኖም ከፍተኛው የኬንያ ፍርድ ቤት ዳኛ ቻቻ መዊታ በዛሬው ችሎት፣ መንግሥት ጣቢያዎቹ ላይ ያስተላለፈውን ዕገዳ እንዲያነሳ አዘው፣ እንዲዘጉ የተላለፈባቸው ጉዳይ በፍ/ቤት እስኪታይ ድረስም፣ መንግሥቱ በመገናኛ ብዙኃን ሥራ ላይ ጣልቃ እንዳይገባ ወስኗል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ