ናይሮቢ —
ጥቅምት 16 2010 ዓ/ም ድጋሚ የተደረገውን የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያን ለሁለተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሓላ ፈጸሙ።
ዛሬ በናይሮቢ፣ ካሳራኒ ስታዲዬም በተደረገዉ ሥነ ሥረዐት ላይ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኬንያውያን የተገኙ ሲሆን ከ40 በላይ መንግሥታት ተወካዮችም ዝግጅቱን ታድመዋል።
ኬንያታ በቃለ መሓላው ወቅት
በሚቀጥሉት 5 ዓመታት የኬንያን ኢኮኖሚ ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገልፀው፣ ኬንያን ለመጎብኘት ወደ ኬንያ የሚጡ አፍሪካዉያን ቪዛ በነፃ እንደሚሰጣቸው ወስነዋል። የምርጫዉን ዉጤት ያልተቀበሉት ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ግን የተቃዉሞ ሰልፍ ተከልክለዉ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ `
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ