በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢኮኖሚ ድቀት በገጠማት ኬንያ ፕሬዝደንቱ እና ባለሥልጣናት የደመወዝ ጭማሪ አገኙ


ናይሮቢ፤ ኬንያ
ናይሮቢ፤ ኬንያ

ኬንያውያን የኢኮኖሚ ድቀት እና የታክስ ጭማሪ በሚያንገላታቸው በዚህ ወቅት፣ የአገሪቱ ፕሬዝደንት፣ ምክትላቸው እንዲሁም ሌሎች ባለሥልጣናት የደመወዝ ጭማሪ ማግኘታቸውን ኤኤፍፒ ተመልክቸዋለሁ ያለውን የመንግስት ዶሴ ጠቅሶ ዘግቧል።

ባለሥልጣናቱ 14 በመቶ ጭማሪ በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ እንደሚያገኙ፣ የአገሪቱ የደመወዝ ኮሚሽን ባቀረበው ሰነድ ላይ ተመልክቷል። ይህም የፕሬዝደንቱን ደመወዝ በወር ወደ 11 ሺህ ዶላር ያደርሰዋል ተብሏል።

የፓርላማ አባላት ደግሞ በወር 5 ሺህ 400 ዶላር እና በተጨማሪም 54 ሺህ ዶላር ለመኪና መግዣ እንዲሁም በወር 2 ሺህ 600 ዶላር መኪናው ለሚያስፈልገው ወጪ እንደሚሰጣቸው ታውቋል።

በኬንያ ዝቅተኛው ደመወዝ 107 ዶላር እንደሆነ የጠቆመው የኤኤፍፒ ሪፖርት፣ የደመወዝ ጭማሪው የመጣው የነዳጅ ዋጋ ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ መጠን በጨመረበት እና መንግስት በነዳጅ ላይ የሚጥለውን ታክስ በእጥፍ በጨመረበት ወቅት ነው። የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው በሌሎች ሸቀጦች ላይ ጭማሪ በማስከተል የኑሮ ውድነቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ሪፖርቱ ጨምሮ ጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG