ኬኒያ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግድያ በመቃወም ዛሬ ማክሰኞ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የተካሄደውን ሰልፍ ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝ በትኖ ቢያንስ ሦስት ተሳታፊዎች ታስረዋል።
በሮይተርስ እና በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መሠረት የሚበዙት ሴቶች የኾኑ ብዙ መቶ ሰዎች "ሴቶችን መግደል ይቁም" የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ በዋና ከተማዋ ሰልፍ አድርገዋል።
ሞምባሳ እና ሎድዋርን በመሳሰሉ ከተሞችም ሰልፍ መካሄዱ ተዘግቧል። ከታሰሩት መካከል በኬኒያ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢሩንጉ ሀተን እንደሚገኙባቸው አምነስቲ ተናግሯል።
በኬኒያ ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት መረጃ መሠረት በሀገሪቱ ከነሐሴ እስከ ጥቅምት በነበረው ጊዜ ብቻ ቢያንስ 97 ሴቶች ተገድለዋል።
መድረክ / ፎረም