በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ መንግሥት ፌስቡክን የመዝጋት ፍላጎት እንደሌለው ሚኒስትሮች አስታወቁ


የኬንያ መንግሥት ፌስቡክን የመዝጋት ፍላጎት እንደሌለው ሚኒስትሮች አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:42 0:00

የኬንያ መንግሥት ፌስቡክን የመዝጋት ፍላጎት እንደሌለው ሚኒስትሮች አስታወቁ

“ፌስቡክ በመድረኩ የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮችን ማስቆም ተስኖታል” በሚል ባለፈው ሳምንት በአንድ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ቢወነጀልም፤ የኬንያ ሚኒስትሮች ግን የዛሬ ሳምንት ከሚካሄደው ምርጫ በፊት ፌስቡክን የማገድ ዓላማ እንደሌላቸው ተናገሩ።

የብሄራዊ ጥምረት እና ውህደት የተባለው ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ በመድረኩ የሚሰራጩትን በዘውግ ማንነት ላይ የተነጣጠሩ የጥላቻ ንግግሮች እንዲቆጣጠር የአንድ ሳምንት ዕድሜ ሰጥቶ፣ ፌስቡክ ያን ማድረግ ካልቻለ ግን ሊታገድ እንደሚችል በመግለጽ አስጠንቅቋል።

የማስጠንቀቂያው ዜና የተሰማው ‘ግሎባል ዊትነስ’ የተባለው የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ባወጣው ሪፖርት፣ “ፌስቡክ ልክ የዛሬ ሳምንት ሰኞ ከሚካሄደው ብሄራዊ ምርጫ አስቀድሞ ባለው ጊዜ ውስጥ እየተደመጡ ያሉትን በጎሳ ላይ የተነጣጠሩ ጥቃቶችን የሚያበረታቱ ማስታወቂያዎች እንዲሰራጩ ፈቅዷል፤” ሲል መውቀሱን ተከትሎ ነው።

ይሁንና የኬንያ የሀገር ውስጥ ሚንስትር ፍሬድ ማቲያንጊ “ጥንቃቄ የጎደለው ውሳኔ ነው ያደረገው” ሲሉ የብሄራዊ ኮሚሽኑን ከሰዋል። “ፌስቡክ አይዘጋም” ሲሉም ለሕዝቡ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

የኬንያ የኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጆ ሙቸሩም ትላንት ሰኞ ለአሜሪካ ድምጽ በስልክ በሰጡት አስተያየት፣ የማቲያንጊን ቃል አስተጋብተዋል። የተነሱት ጉዳዮች ትክክለኛ መሆናቸውን አምነው፣ “የተባለውን እርምጃ መወሰድ ፌስቡክን ለመዝጋት ግን አያበቃም” ብለዋል።

አስከትለውም፤ “እኔ ያልደገፍኩት ሐሳብ ቢኖር እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲከሰት የመጀመሪያው አማራጭ መሆን ያለበት የማሕበራዊ ትስስር መረቡን መዝጋት ነው። ይህ ደግሞ ከእኛ የማስፈጸም ስልጣን ውጭ ነው።” ብለዋል።

ከፌስቡክ እና ከሌሎች በርካታ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ጋራ ስንሠራ ሲሠሩ መቆየታቸውንም ጠቅሰው “ፌስቡክ ለምሳሌ በዚህ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ቁጥራቸው ከ37, 000 በላይ የሚደርሱ የትንኮሳ ይዘት ያላቸው አስተያየቶችን ከገጹ እንዲሰረዙ አድርጏል።'' ብለዋል።

በሌላ በኩል ፌስቡክ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ 13 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች እንዳሉባት በምትገመተው ኬንያ ቁጥጥር ሳያደር ያመለጡት የጥላቻ ይዘት ያላቸው ንግግሮች መኖራቸውን አምኗል።

የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ ቃል አቀባይ ሲናገሩ ፤”አንዳንድ ቆስቋሽ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች ሳይታዩ መውጣታቸውን እና ለዚህም በሰው እና በቴክኖሎጂ ተፈጸሙ ያሏቸውን ግድፈቶች ለመከላከል እርምጃዎችን ወስደናል” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG