በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤሪክ አሲንታ ጠባሳ - በኬንያ የጋዜጠኞች ጥቃት አስታዋሹ


የኤሪክ አሲንታ ጠባሳ - በኬንያ የጋዜጠኞች ጥቃት አስታዋሹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00

የኤሪክ አሲንታ ጠባሳ - በኬንያ የጋዜጠኞች ጥቃት አስታዋሹ

የኤንቲቪ የቪዲዮ ጋዜጠኛ የኾነው ኤሪክ ኢሲንታ፣ ባለፈው መጋቢት ወር፣ ክሥተቱን ለመዘገብ የተገኘበትን የተቃውሞ ምስሎች፣ በእጅ ስልኩ ላይ በመመልከት ላይ ነው።

በተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ በተጠራው ተቃውሞ፣ ሰልፈኞች፥ እየጨመረ በመጣው የኑሮ ውድነት መማረራቸውን ገልጸዋል።

በሰላም የተጀመረው ሰልፍ፣ ወዲያውኑ ወደ ብጥብጥ ተቀይሯል። ኤሪክ ኢሲንታ ዕለቱን እንዲህ ያስታውሳል። “አስለቃሽ ጢሱ፣ በርግጥ የተወረወረው በእኛ ላይ ነበር። በወቅቱ እያሳለን ነበር። እንዲህ ሲከፋብን ለመጀመሪያ ጊዜ ስለኾነ፣ የካሜራ ባለሞያ ባልደረቦቼን፥ እባካችሁ ከእዚኽ እንሒድ እያልኋቸው ነበር፤” ብሏል፡፡

ጋዜጠኞች፣ ፖሊስ፥ እነርሱ ወዳሉበት እየተጠጋ የአስለቃሽ ጢሱን ሲለቅ፣ ባሉበት ተሸከርካሪ ላይ፣ መቅጃዎቻቸውን አስተካከለው ጋዙ የሚያርፍበትን ትክክለኛ ቦታ አነጣጥረው ለመቅረጽ እየሞከሩ ነው፡፡

“ዘወር ብዬ ሊወድቅ የነበረውን ካሜራ ለመያዝ ስሞክር፣ የተተኮሰው አስለቃሽ ጢስ መታኝ። ከዚያ በኋላ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም፤” ሲል ገልጿል ኢሲኒታ፡፡

ለጋዜጠኞች እውቅና የሚሰጠውና የፕሬስ ነፃነትን ይዞታ የሚከታተለው፣ ብሔራዊ የሚዲያ ካውንስል፣ የራሱንና የሌሎችንም ጨምሮ ጉዳዩን እየተከታተለው እንዳለ ይገልጻል፡፡ የኬንያ ሚዲያ ካውንስል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴቪ ኦምዎዮ፣ “ለዋና መርማሪው ፖሊስ ጽፈናል። ጉዳዩን ሰንደን አስገብተናል። አንድ በአንድ እየተክታተልን ነው።” ብለዋል፡፡

የኬንያ ፖሊስ ዋና ተቆጣጣሪ፣ ከተቃውሞው በኋላ ይቅርታ ጠይቀው፣ ማንኛውም ብልሹ አሠራር እንደሚስተካከል ተናግረዋል፡

የብሔራዊ ሚዲያ ካውንስሉ፣ ጋዜጠኞች፥ ለዘገባቸው የሚመጥኑ፣ ለምሳሌ በቅርቡ “ከዓለም ፍጻሜ አምልኮ” ጋራ በተያያዘ፣ ከጅምላ መቃብር የተገኙትን በርካታ አስከሬኖች ጉዳይ የመሳሰሉ ኹነቶችን እየተከታተሉ መዘገብ የሚያስችላቸውን ዕድል የሚያገኙበትን መንገድ ለማረጋገጥ እየሠራ ነው፡፡ ባለሥልጣናት ግን፣ ለጋዜጠኞች ክፍት እንዳይደረግ ሞክረዋል፤ ሲሉ ኦምዎዮ ይናገራሉ፡፡

ኦምዎዮ ይህንኑ ሲያስረዱ፣ “እንዲህ ዐይነቱ አሠራር ተቀባይነት እንደሌለው ለመንግሥት አስታውቄያለኹ። ችግራቸው ይገባኛል፤ ነገር ግን የሚዲያ ማዕከል አቋቁመው ተከታታይ መግለጫ መስጠት አለባቸው። በሩን ለሚዲያ ክፍት የማታደርግ ከኾነ፣ የአሉባልታው በር ወለል ብሎ ይከፈታል። አሉባልታ ደግሞ አገር ሊያጠፋ ይችላል። ሰዎች ወሬን የማጣራት ልምድ የላቸውም፤” ብለዋል፡፡

የኬንያ መንግሥት ቃል አቀባይ፣ ከቪኦኤ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ አልሰጠም፡፡ “ኬንያ፣ በዓለም የተስፋፋው የሐሰት እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሰለባ ኾናለች፤” የሚሉት፣ በአጋ ካን ዩኒቨርስቲ፣ የሚዲያ ክፍለ ትምህርት ተቋም ናንሲ ቡከር ናቸው፡፡

ናንሲ፣ “ሐሰተኛ ወሬ በርክቷል። በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ብሶበት ነበር። የዚያን ጊዜውን ተጽእኖ አሁን ድረስ እያየን ነው፤” ይላሉ፡፡ተቃውሞን ለመዘገብ ሲሔድ፣ በአስለቃሽ ጢስ በደረሰበት ጉዳት ለቆሰለው ኢሲንታ፣ አብሮት የቀረው ጠባሳ፥ የኬንያ ጋዜጠኞች በየዕለቱ ምን ያህል አደጋዎችን እንደሚጋፈጡ አስታዋሽ መኾኑ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG