በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ የጅምላ መቃብሩ ብሔራዊ መታሰቢያ ሊሆን ነው


ፎቶ ፋይል፡ የፖሊስ መኮንኖች አስከሬን እያወጡ
ፎቶ ፋይል፡ የፖሊስ መኮንኖች አስከሬን እያወጡ

ክርስቶስን እንድታገኙ ተራቡ በሚል በቤተ ክርስቲያን መሪያቸው ተነግሯቸው ሕይወታቸውን ያጡበትን እና እስከአሁን 250 የሚሆኑ ስዎች ከጅምላ መቃብር ውስጥ የወጡበትን ሥፍራ ወደ ብሔራዊ መታሰቢያነት እንደሚቀይር የኬንያ መንግሥት አስታውቋል።

በሰላማዊ ውቅያኖስ ባህር ዳርቻ በሚገኝ ደን ውስጥ ከሚገኘውና 325 ሄክታር ስፋት ካለው ሥፍራ በርካታ የጅምላ መቃብሮች ላለፉት በርካታ ሳምንታት መገኘት ኬንያውያንንና የተቀረውን ዓለም አስደንግጧል።

ተከታዮቹ ሕይወታቸውን እንዲያጡ አድርጓል የተባለው የቤተክርስቲያኑ መሪ ፖል ማከንዚ በርካታ ክሶች ቀርበውበታል።

መርማሪዎች ትናንት ሦስተኛ ዙር አሰሳቸውን ሲጀምሩ፣ ተጨማሪ ዘጠኝ አስከሬኖችን ማግኘታቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መራባቸው ለሞት እንዳበቃቸው ቢታመንም፣ ሕጻናትን ጨምሮ አንዳንዶቹ ሟቾች ግን እንደታነቁ፣ ድብደባ እንደደረሰባቸው እንዲሁም አየር እንዲያጡ መደረጉን በመንግሥት የተካሄደው የአስከሬን ምርመራ ውጤቶች አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG