በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይሮቢ ሥራ የገቡም ያልገቡም አሉ


ተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ
ተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ

ኬንያዊያን ባለፈው ሣምንት የተካሄደውን ምርጫ ውጤት እንዲቃወሙና ዛሬ - ሰኞ ከየቤታቸው ሳይወጡ እንዲውሉ ተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አስተላልፈው የነበረ ሲሆን አንዳንዶች ጥሪውን ተቀብለው ማደማቸውና ብዙዎች ደግሞ ወደ ሥራ መግባታቸው ታውቋል።

ኬንያዊያን ባለፈው ሣምንት የተካሄደውን ምርጫ ውጤት እንዲቃወሙና ዛሬ - ሰኞ ከየቤታቸው ሳይወጡ እንዲውሉ ተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አስተላልፈው የነበረ ሲሆን አንዳንዶች ጥሪውን ተቀብለው ማደማቸውና ብዙዎች ደግሞ ወደ ሥራ መግባታቸው ታውቋል።

ለአንድ ሣምንት የዘለቀው የናይሮቢ መንገዶች ጭርታ የገፈፈለት ቢመስልም ከነኀሴ አንዱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጋር ተያይዞ የተነሣው ውዝግብ አበቃለት ማለት ግን አይደለም።

ምርጫው ተጭበርብሯል በሚለው አቋማቸው የፀኑት ተቃዋሚዎች ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ማሸነፋቸው በይፋ ቢገለፅም “አሻፈረን፤ ሽንፈትን አንቀበልም” ብለዋል።

የኬንያታ ማሸነፍ ወሬ ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ በአንዳንድ የናይሮቢ መንደሮችና በሃገሪቱ ምዕራባዊ አካባቢዎች የዋናው ተቀናቃኝ ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ላይ ሰንብተዋል።

በናይሮቢ ማጣሬን የመሳሰሉ ቀበሌዎች ከተቃውሞውና ከሁከቱ የበዛው የተስተዋለባቸው ሲሆኑ አንዳንድ ወጣቶች የምርጫውን ውጤት እና የተቃውሞው ጎራ መፃዒ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ለመነጋገር እዚህም እዚያም ይሰባሰባሉ።

ናሳ በሚል ምኅፃር የሚጠራው የተቃዋሚው “ብሄራዊ የላቀ ጥምረት” መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጠንካራ ድጋፍ ወዳላቸው ኪቤራ መንደር ትናንት - ዕሁድ ሄደው ተሰብስበው ይጠብቋቸው ለነበሩ በሺሆች ይቆጠራሉ ለተባሉ ደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገው ነበር።

ኦዲንጋም የጥምረታቸው የናሳ አባላትም ምርጫውን በገዥው ጁቤሊ ፓርቲ ተሰርቀናል የሚለውን መልዕክታቸውን አጠንክረው አሰምተዋል።

የመንግሥቱ የደኅንነት ኃይሎሀች ደጋፊዎቻቸውን መግደላቸውንና ሳይጠየቁ መታለፋቸውንም እየገለፁ ከስሰዋል፤ ሰዉ ዛሬ ሥራ እንዳይገባም ጠይቀዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባስተላለፉት መልዕክት “ምርጫው አብቅቷል፤ ኬንያዊያን ወደየሥራቸው ሊመለሱ ይገባል” ብለዋል። ተቃዋሚዎችም ውጤቱን እንዲቀበሉና ቅሬታ ያላዡው ጉዳያዡውን ወደ ፍርድ ቤት እንዲወስዱ መክረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ናይሮቢ ሥራ የገቡም ያልገቡም አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG