በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ በታክስ ጭማሪ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተቃውሞው ቀጥሏል


በኬንያ ረቂቅ የታክስ ጭማሪ አዋጅን በመቃወም በናይሮቢ ኬንያ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፤ እአአ ሰኔ 20/2024
በኬንያ ረቂቅ የታክስ ጭማሪ አዋጅን በመቃወም በናይሮቢ ኬንያ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፤ እአአ ሰኔ 20/2024

በኬንያ ረቂቅ የታክስ ጭማሪ አዋጅን በመቃወም በናይሮቢ እና በሌሎችም አካባቢዎች በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።

የታክስ ጭማሪውን በመቃወም ለወራት በማኅበራዊ ሚዲያ ሲደረግ የነበረው ዘመቻ፣ ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተቀይሯል።

የታክስ ጭማሪው የሚደረገው ብድርን ለመክፈል እና ለልማት ሥራዎች እንደሆነ መንግስት ይገልጻል።

መንግስት ከረቂቅ አዋጁ ውስጥ የተወሰኑትን እንደሚተው ቢያስታውቅም፣ ዛሬ ሐሙስ የተቃውሞ ሰልፉ መቀጠሉ ታውቋል።

የታክስ ጭማሪው በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የሚደረግ ሲሆን፣ በነዳጅ ላይ ሊጨመር የታሰበው 9 ሺልንግ ለፈረሱ መንገዶች መጠገኛ እንደሚሆን የአዋጁ አርቃቂዎች አስታውቀዋል።

መንግስት በተጨማሪም አካባቢን ለመጠበቅ በሚል ታክስ ለመጣል ያቀደ ሲሆን፣ ይህም የፕላስቲ ውጤቶች የሚያስከትሉትን ብከላ ለመከላከልና እንደሆነ አስታውቋል።

ብሔራዊ ሸንጎው ረቂቅ አዋጁን በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያጸድቅ ሲጠበቅ፣ ኬንያውያን ግን በተቃውሞው እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG