ዋሺንግተን ዲሲ —
የኬንያው ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታና የሶማልያው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ /ፋርማጆ/- በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተባባሪነት በዛሬው ዕለት በኬንያ ውይይት ማድረጋቸው ተዘገቧል።
የሦስቱ ሀገሮች መሪዎች በተጨማሪም - ሽብርተኝነትን ለመከላከልና በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅነንትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
ኬንያ እና ሶማልያ በባህር ክልል ወሰን ይገባኛል ጥያቄ ሰሞኑን አለመግባባት ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ሊቀ መንበር እንደመሆናቸው - በኬንያ እና ሶማልያ መካከል የተፈጠረውን አመለግባባት ለማስወገድ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ