በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከረጅም ዓመታት በኋላ በኬንያ መታወቂያ ያገኙ የሾና ማኅበረሰብ አባላት ደስታቸውን እየገለፁ ነው


ኬንያ ውስጥ ዜግነት አልባ ሆነው ለዐስርት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ፍቃድ የተሰጣቸው የሾና ማኅበረሰብ አባላት ደስታቸውን እየገለፁ ነው። ኬንያ ባለፈው ወር በሃገሯ ከ50 ዓመታት በላይ ለኖሩ የሾና ማኅበረሰብ አባላት ሕጋዊ ዜግነት የሰጠች ሲሆን ይህንን መታወቂያ የተቀበሉ የማኅበረሰቡ አባላት፤ ከዚህ ቀደም ሲገጥማቸው የነበሩ ችግሮች ከዚህ በኋላ እንደተቀረፉ ተስፋ በማድረግ ደስታቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው።

ያለ ኬንያ የመታወቂያ ወረቀት የባንክ ሂሳብ ከማንቀሳቀስ ጀመሮ ለረጅም ዓመታት በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደነበሩም ገልፀው የኬንያ መንግሥት በመጨረሻ በሰጠው ውሳኔም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የሾና ማህበረሰብ አባላት እ.አ አ በ1930 ዓ.ም ከዙምባብዌ ወንጌል ለመስበክ የመጡ ሲሆን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት መታወቂያ በኬንያ አልነበራቸው።

XS
SM
MD
LG