በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ የአስገድዶ መድፈርና የወሲብ ጥቃት ተግባር ጨምሯል


ኬንያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መዛመትን ለመቆጣጠር ሲባል፣ ሰዎች በቤታቸው አካባቢ እንዲወሰኑ ከተገደቡበት ጊዜ ወዲህ፣ በልጃገረዶች ላይ አስገድዶ የመድፈርና የወሲብ በደል የመፈጸም ተግባር እየጨመረ መሄዱን፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣኖችና የረድኤት አገልግሎቶች አስገንዝበዋል። አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ ዓይነቱን በደል የሚፈጽሙትም፣ ዘመዶቻቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ኬንያ ውስጥ በቫይረሱ ምክንያት፣ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉበት ጊዜ አንስቶ፣ ልጆች በቤታቸው አካባቢ በመሆናቸው፣ ሊጠብቋቸው በሚገባ ዘመዶች ሳይቀር ስለሚደፈሩ፣ አንዳንድ ናይሮቢ ያሉ፣ መሄጃ ያጡ ሴቶች የሚጠጉባቸው ቦታዎች፣ ከቤተሰቦቻቸው በሸሹ ልጆች እንደተጣበቡ ተገልጿል።

የኬንያ የጤና ሚኒስቴር፣ በሀገሪቱ ዙርያ ቢያንስ 5,000 የሚሆኑ ሴቶች፣ የወሲብ ጥቃት እንደተፈጸመናቸው የሚያሳዩ ዘገባዎች እንደደረሱት ገልጿል። ከነሱም 65 ከመቶዎቹ፣ ከ 18 ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ልጆች መሆናቸውን፣ አብዛኞቹ ደግሞ በድኅነት የሚኖሩ እንደሆኑ የሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ ተናግሯል።

XS
SM
MD
LG