በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ በአንድ ት/ቤት በደረሰ የእሳት አደጋ 17 ተማሪዎች መሞታቸው ተገለጠ

በኬንያ በአንድ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት በትላንትናው ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ 17 ተማሪዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ሌሎች 13 የሚሆኑ ክፉኛ መጎዳታቸው ታውቋል።

የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀሰውም ሊያሻቅብ እንደሚችል ፖሊስ ስጋቱን ገልጿል። የእሳቱ መነሻ ምክንያትንም እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል።

ኒየሪ በተሰኘው አውራጃ በሚገኘው በዚህ ት/ቤት ውስጥ አደጋው በደረሰበት ምሽት 150 የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች እንቅልፍ ላይ እንደነበሩም ተገልጿል።

በኬንያ በትምህርት ቤት የሚደርሱ የእሳት አደጋዎች እየተለመዱ መጥተዋል ያለው የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ፣ ወላጆች ልጆቻቸው ወደ ት/ቤት በመመላለስ የሚያጠፉትን ጊዜ ለማስቀረት በአዳሪ ት/ቤት እንደሚያስመዘግቡ አመልክቷል።

በትምህርት ቤቶቹ የሚደርሱ የእሳት አደጋዎች መነሻ በአደንዛዥ ዕጽ ተጽእኖ ሥር መሆንና እና ከመጠን በላይ መጨናነቅ በሚያባብሱት ሁኔታዎች ምክንያት ሆን ተብሎ በሚለኮስ እሳት መሆኑን በሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር የተሰራ ጥናት አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG