በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዝደንት ኦባማ የአፍሪካ ጉዞ ንግድን ያሳልጣል፣ በጎ ገጽታ ይገነባል ይላሉ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር


Kenya Obama
Kenya Obama

የዩናይትድ ስቴይትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ኬንያን መጎብኘታቸው ለመንግስታቸው ታላቅ ድጋፍእንደሚሆን የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ። የፕሬዝደንቱ ጉብኝትም ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ ይዞይመጣል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ድምጹ ቪንሰንት ማኮሪ በናይሮቢ ሚኒስትሯን ሐሙስለት የኬንያ የካቢኔ ሚኒስትር አሚና ሞሃመድንአነጋግሯል።

ሚኒስትሯና መንግስታቸው በፕሬዝደንት ኦባማ የአፍሪካ ጉዞ ፍጹም ደስተኛ ናቸው። በሀገሪቱ የተስፋ ብርሃንይፈነጥቃል፤ ለፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታዳደርም በጎ ገጽታን ያቀርባል ሲሉ ለአሜሪካ ድምጹ ቪንሰንትማኮሪ ገልጸዋል።

“መምጣታቸው አስተዳድራችንን በጎ ገጽታን ያላብሰዋል። በርትተን የምንሰራና የሀገራችን ጉዳይ በእጅጉየሚያነቃቃን፣ አመራራችን ብቁ መሆኑን ያመላክታል። ከዚያ በተጨማሪ ኬንያ ባለፉት ጥቂት ዓመታትያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች ያጎላል” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴይትስና ኬንያ ግንኙነት ሁል ጊዜ የጫጉላ ሽርሽር አይነት አይደለም። አንዳንዴ መፋተግናውጥረት የታየበት ግንኑነት ነው። በተለይ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ በአለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰረትባቸው ግንኙነት ኡሻክሮ ነበር። ICC ኬንያዊያኑ መሪዎች በ2000ሽህዓም የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ የተፈጠሩ ሁከቶችን አስተባብረዋል በሚል ነው።

በአሁኑ ጊዜ ያ የውጥረት ዘመን አልፏል። ያለፈው ደግሞ አልፏልና ወደ መዝገብ ቤት ያመራል ማለት።ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በነገውለት ኬንያ መዲና ናይሮቢ ይገባሉ። የዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ጉባዔንይከፍታሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ከዓለም ዙሪያ የንግድ ስራ ድርጅቶችን የሚመሩ ሁሉ ይሰባሰባሉ። የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚናሞሀመድ፤ ከዚህ ጉባዔ የሚገኙ የመዋእለ ንዋይ ፍሰቶች ያጓጓቸዋል።

ከንግድ ባሻገር በፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጉዞ ከፍተኛ ትኩረት የሚያገኘው ጉዳይ የሀገር ደህንነት ነው። ኬንያከሶማሊያ ጋር ድንበር ትጋራለች። በሶማሊያ መሰረቱን ያደረገው የእስልምና ታጣቂ ቡድን አልሸባብበተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርስባትም ቆይቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና ሞሀመድ አሜሪካ እንዲህ ያሉ ጥቃቶችን ለመከላከል ኬንያን ስታግዝ ቆይታለች ይላሉ “በተለይ በደህንነት ዙሪያ ያለን ትብብር ታሪካዊ ነው። ሁልጊዜም የነበረ፤ በሰፊው ያጠናከርንውና፤ ባለፉትጥቂት ዓመታት ደግሞ የኛም ጥቃት የሌላው አለም ጥቃት በመሆኑ መተባበራቸን አልቀረም። አለመረጋጋትበአንድ ስፍራ ብቻ የተወሰነ ተጽዕኖ እንደሌለው በስፋት ይታወቃል። “

ኬንያ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችና ሁከቶችን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች።በቡሩንዲ ፕሬዝደንት ፒየር እንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን መወዳደራቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሱግጭቶችን ለማብረድ ስትሰራ ቆይታለች።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስት በአካባቢው ሀገሮች ሰላም እንዲሰፍን፣ በሶማሊያ መንግስቱ እንዲጠናከር፣በደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ግጭቱ እንዲቆም ሃገራቸው ተግታ እንደምትሰራ ገልጸዋል።

የፕሬዝደንት ኦባማ የአፍሪካ ጉዞ ንግድን ያሳልጣል፣ በጎ ገጽታ ይገነባል ይላሉ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG