በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩቶና ኦዲንጋ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ


የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከቀድሞው ዋና ተፎካካሪያቸው ከራይላ ኦዲንጋ ጋራ
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከቀድሞው ዋና ተፎካካሪያቸው ከራይላ ኦዲንጋ ጋራ

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከቀድሞው ዋና ተፎካካሪያቸው ከራይላ ኦዲንጋ ጋራ በፖለቲካ ጉዳዮች ትብብር ለማድረግ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ወገኖች እየጨመረ ያለውን የሃገሪቱን ዕዳ እና ሙስናን ጨምሮ ሌሎቹንም ሃገሪቱን የገጠሟትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል።

ሩቶ የግብር ጭማሪ እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸውን ተከትሎ በሃገሪቱ በተነሳው ተቃውሞ ቢያንስ 60 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የነበራቸው የሕዝብ ድጋፍም እያሽቆለቆለ መጥቷል።

ተቃውሞው በመበርታቱም ሩቶ ከተቃዋሚያቸው ከኦዲንጋና ከበርካታ የፓርቲ አባሎቻቸው ጋራ”ሰፊ መሠረት ያለው” መንግሥት ለመመስረት እንዲሠሩ አስገድዷቸዋል። ይህንን ስምምነትም ዛሬ በይፋ በመፈረም ሃገሪቱ የገጠማትን ችግሮች ለመቅረፍ በጋራ እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።

ጉምቱ የተቃዋሚ ፖለቲከኛው ራይላ ኦዲንጋ በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አምስት ጊዜ ተሳትፈው ሳይቀናቸው ቀርቷል።

ስምምነቱ በሃገር ውስጥ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ያለመ እንደሆነ የ80 ዓመቱ ኦዲንጋ አስታውቀዋል። ሩቶ በበኩላቸው ስምምነቱ “ነፃነትና መልካም አጋጣሚዎች ለሁሉም መድረሳቸውን ማረጋገጫና ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚወስድ መንገድም ነው” ብለዋል።

የፖለቲካ ተንታኞች ስምምነቱን "እየተንኮታኮተ ያለው አገዛዝ እንዲያንሰራራ የተደረገ ሙከራ" ሲሉ ገልጸውታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG