በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ከፍተኛ ፍ/ቤት የስደተኞች መጠለያ እንዳይዘጋ በማገዱ ተደነቀ

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም እጅግ ግዙፍ የሚባለው የስደተኞች መጠለያ ሠፈር እንዳይዘጋ ማገዱን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች አሞግሰዋል።

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም እጅግ ግዙፍ የሚባለው የስደተኞች መጠለያ ሠፈር እንዳይዘጋ ማገዱን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች አሞግሰዋል።

መንግሥት ከሦስት መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ያስጠለለውን ዳዳብ የሚባለውን መጠለያ ሰፈር እንደሚዘጋ አስታውቆ ነበር።

አብዛኞቹ በሠፈሩ ውስጥ የተጠለሉት ስደተኞች ከሶማሊያ የገቡ ሲሆኑ መንግሥቱ ሊዘጋው የወሰነው ለሀገሪቱ ፀጥታ አደጋ ይደቅናል በሚል እንደነበረ ገልጿል።

ይሁንና ሠፈሩን የመዝጋቱ ውሣኔ የኬንያን ሕገ-መንግሥትና ዓለም አቀፍ ውሎችን ይፃረራል ያሉት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኛ እንዳይዘጋ ትላንት ባሰሙት ውሣኔ አግደዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኬንያ ከፍተኛ ፍ/ቤት የስደተኞች መጠለያ እንዳይዘጋ በማገዱ ተደነቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:24 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG