በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ መንግሥት ተቃውሞዎቹን ተከትሎ ትምህርት ቤቶችን ዘጋ


የተቃውሞ ሰልፎችን ለመበተን፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ በመጠቀሙ፣ አንዳንዴም በቀጥታ ወደ ሕዝቡ በመተኮሱ፣ ሁከቱ ተባብሶ እንደነበር ተመልክቷል፡፡
የተቃውሞ ሰልፎችን ለመበተን፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ በመጠቀሙ፣ አንዳንዴም በቀጥታ ወደ ሕዝቡ በመተኮሱ፣ ሁከቱ ተባብሶ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

የኬንያ መንግሥት፣ በአገሪቱ የተከሠተውን የኑሮ ውድነት ምክንያት በማድረግ፣ ለሦስት ቀናት የተካሔደውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ በዋና ከተማው እና በሌሎች ሁለት አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን፣ ዛሬ ረቡዕ ዘግቷል፡፡

የኬንያ ተቃዋሚዎች ሰልፉን የጠሩት፣ ባለፈው ወር፣ የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥት፣ ያሳለፈውን የግብር ጭማሪ ተከትሎ ነው፡፡

ባለፈው ነሐሴ የተመረጡት ፕሬዚዳንት ሩቶ፣ የድኾችን ጥቅም ለማስጠበቅ ቃል ቢገቡም፣ በእርሳቸው አስተዳደር፣ የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

መንግሥት፣ በዓመት 1ነጥብ4 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝለት የሚጠብቀው የነዳጅ እና የመኖሪያ ቤት ቀረጥ፣ እያደገ የመጣውን የብድር ክፍያ ለመቋቋም እና ለሥራ ፈቃድ ተነሣሽነቶች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስገኝ ገልጿል፡፡

በዚኽ ወር፣ ለሁለት ዙር የተካሔዱትን የተቃውሞ ሰልፎች ለመበተን፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ በመጠቀሙ፣ አንዳንዴም በቀጥታ ወደ ሕዝቡ በመተኮሱ፣ ሁከቱ ተባብሶ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ሲካሔዱ በሰነበቱት ተቃውሞዎች፣ 15 ሰዎች ሲገደሉ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ታስረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG