በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩቶ ከፊል ካቢኔያቸውን ይፋ አደረጉ


የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ

ከሃገራቸው ሕዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከፊል አዲስ ካቢኔ ዛሬ ዓርብ አቋቁመዋል።

ሩቶ ባለፈው ሳምንት ካቢኔያቸውን በትነው ሰፊ መሠረት ያለው መንግስት እንደሚያቋቁሙ ቃል ገብተው ነበር።

ለተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎቹ ግን እርምጃቸው በቂ አልነበረም። በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የሚገናኙትና የሩቶን መንግስት እረፍት የነሱት በአብዛኛው ወጣት ተቃዋሚዎች፣ ሩቶ ሥልጣን ካልለቀቁ ተቃውሟቸውን እንደሚቀጥሉ ዝተዋል።

ሩቶ 11 አዲስ የካቢኔ አባላትን ሥም ዝርዝር ይፋ አድርገዋል።

ባለፈው አንድ ወር የተከሰተው ተቃውሞን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሰፊ መሠረትና ሁሉም ዜጎች የሚሳተፉበት ብሔራዊ መሻሻልና ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ሩቶ ዛሬ አስታውቀዋል።

አዲስ ተሾሙ የተባሉት የካቢኔ ዓባላት ግን በአብዛኛው የቀድሞው መንግስት ዓባላት መሆናቸው ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG