በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የኬንያ ፖሊስን የሃይል እርምጃ አወገዙ


ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ ፖሊስ ሰልፎኞችን ሲበትን
ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ ፖሊስ ሰልፎኞችን ሲበትን

በኬንያ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፖሊስ በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ የሚወስደውን ዘግናኛ ያሉትን እርምጃ አውግዘዋል፡፡

ሰኞ ዕለት በተካሄደው የመንግሥት ተቃውሞ ሰልፍ ወቅት አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሲገደል 31 የሚሆኑ ፖሊሶች ተጎድተዋል፡፡

በዚሁ በተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ በተጠራው ሠልፍ ወደ 240 የሚሆኑ ሰዎች ተይዘዋል፡፡

የኬንያው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሌሎች መብት ተሟጋች ቡድኖች ጋር በመሆን ባወጣው መግለጫ በኬንያ ፖሊስ የተፈጸመው ከልክ በላይ የሆነ የሃይል እርምጃና ክልከላ አግባብ የለውም ብሏል፡፡

በኪሲሙ ከተማ አንድ የማሴኖ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደሉን መግለጫው አመልክቷል፡፡ ግድያውን በመቃወም ተማሪዎች ትናንት ሰልፍ አድርገዋል፡፡

ፖሊስ በበኩሉ ሰልፈኞቹ ጣቢያቸውን በመውረር አባሎቹ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል ብሏል፡፡ 10 የፖሊስ መኪኖችም ተሰባብረዋል ተብሏል፡፡

ባለፈው ነሃሴ በምርጫ ሥልጣን የተቆጣጠሩት ዊሊያም ሩቶ አስተዳደራቸውን በተመለከተና እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድንነት በመቃወም የተቃዋሚ መሪው ራይላ ኦዲንጋ በየሳምንቱ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አድርገዋል፡፡

XS
SM
MD
LG