በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ የተቃዋሚ መሪዎች ጥሪ እና ምላሹ


የኬንያ ፖሊሶች ናይሮቢ ውስጥ ኪቤራ በሚባለው ሰፈር ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ሲተኩሱ 
የኬንያ ፖሊሶች ናይሮቢ ውስጥ ኪቤራ በሚባለው ሰፈር ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ሲተኩሱ 

በኬንያ በዋና ከተማዋ በናይሮቢ በፖሊስ እና ድንጋይ በወረወሩ ሰልፈኞች መካከል የተወሰኑ ግጭቶች ቢታዩም፣ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ጸረ መንግሥት እንቅስቃሴው እንዲጠናከር ተቃዋሚዎች ያስተላለፉትን ጥሪ ኬንያውያን በአመዛኙ ችላ ብለውታል፡፡

ዛሬ ፖሊሶች ናይሮቢ ውስጥ የተቃዋሚዎች ጠንካራ ይዞታ በሆነውና ኪቤራ በሚባለው የድሆች ሰፈር ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ሲተኩሱ የኤኤፍፒ ዘጋቢዎች አይተዋል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች ግን ባለፉት የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ዛሬ ግጭት ስለመከሰቱ የወጣ ዘገባ የለም፡፡

ዋናው የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ በዚህ ሳምንት ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ይታወቃል፡፡

ትናንት ረቡዕ በተካሄደው ተቃውሞ የስድስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ከተጎጂ ቤተሰቦች ማጣራቱን የኬንያው የአምነስቲ ኢነተርናሽናል ቅርንጫፍ ገልጿል፡፡

ካለፈው መጋቢት ወዲህ ከተቃውሞው በተያያዘ 20 ሰዎች መሞታቸውን ከመንግስት እና ሆስፒታሎች የወጡ መረጃዎች ያመለከቱ ሲሆን ብጥብጡ ኬንያውያንን እና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ አሳስቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG