በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ኡሑሩ የገዢው ፓርቲ አባላት ብቻ የተገኙበት የምክር ቤት ስብሰባ አካሄዱ

የኬንያውን የምርጫ ድራማ ቀጣይነት ያመላከተ በሚመልስ ሁኔታ፣ ፕሬዚደንት ኡሑሩ ኬንያታ፣ የገዢው ፓርቲ አባላት ብቻ የተገኙበትን የምክር ቤት ስብሰባ ማካሄዳቸው ተሰማ።

የኬንያውን የምርጫ ድራማ ቀጣይነት ያመላከተ በሚመልስ ሁኔታ፣ ፕሬዚደንት ኡሑሩ ኬንያታ፣ የገዢው ፓርቲ አባላት ብቻ የተገኙበትን የምክር ቤት ስብሰባ ማካሄዳቸው ተሰማ።

“በከባድ ትግል የተገኘው ሠላምና መረጋጋት በማንም እንዲደናቀፍ መንግሥት ትዕግስት እንደሌለው በበቂ ሁኔታ ግልፅ ማድረግ እፈልጋለሁ” ያሉት ፕሬዚደንት ኬንያታ፣

“ኬንያውያንም ይህ ነፃና ብቃት ያለው ሂደት፣ በፀረ ሠላም ኃይሎች እንዲኮላሽ ከቶም አይፈቅዱም” ብለዋል።

ተቃዋሚ የምክር ቤቱ አባላትም፣ ያለፈውን የነሐሴ ሁለት ቀን የምርጫ ውጤት ውድቅ ያደረገውን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት በማድረግ፣ የኬንያታን ህጋዊነት በመጠየቅ ስብሰባውን እየጣሉ ወጥተዋል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔና ይልቁንም ዳኞቹን፣ ኬንያታ፣ «ሸፍጠኞች» ብለው መዝለፋቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG