በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ውሳኔ


የአለፈዉ ዓርብ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ውሳኔ በኬንያታ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታ ሲያሳድር በተቀናቃኛቸዉ በራይላ ደጋፊዎች ዘንድ ግን ልዩ ደስታን ፈጥሯል።

የአለፈዉ ዓርብ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ውሳኔ በኬንያታ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታ ሲያሳድር በተቀናቃኛቸዉ በራይላ ደጋፊዎች ዘንድ ግን ልዩ ደስታን ፈጥሯል።

ሁለቱ ተፎካካሪዎች ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ ወደ ምርጫ ቅስቀሣ እንደሚገቡ የተናገሩ ሲሆን ፕሬዚደንት ኬንያታ ግን ባለፈው ዓርብ ውሳኔውን የሰጡትን ዳኞች በመዛለፋቸዉ ከኬንያ የፍርድ ቤት ዳኞች ማኅበር ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።

በስድሥት የኬንያ ዳኞች የተላለፈው የኬንያ የምርጫ ውጤት ውሳኔ በኬንያውያን ዘንድ ልዩ ስሜትን ፈጥሮአል። የተቀናቃኙ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች የምርጫው መደገም ፍትሃዊ የሆነ የምርጫ ዙር እንዲካሄድ ይረዳል በማለት የዳኞቹን ውሳኔ በፀጋ ተቀብለዋል።

ለዚህም ዓርብ ዕለት ውሳኔው በይፋ ሲነገር በኦዲንጋ የትውልድ ቦታ ኪሱሙ ከተማ፣ እንዲሁም በተለያዩ የናይሮቢ ቦታዎች ነዋሪዎች ወጥተው ደስታቸውን ገልፀዋል። ብዙዋች ደግሞ የዳኞቹ ውሳኔ ያልተገመተ በመሆኑ ጉዳዩን በኬንያ አነጋጋሪ እንዲሆን አድርጎል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ውሳኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG