በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔና የምርጫ ኮምሽኑ


“የ2017ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሕገ መንግስቱና በጽሁፍ በተቀመጡ የአገሪቱ የምርጫ ሕጎች ድንጋጌ መሠረት ያለመካሄዱን ነው ያጤንነው። ግልጽም፣ በማረጋገጫ ሊደገፍ የቻለም አይደለም። በዚህ የሕጉ አግባብ እና በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 83 የሕግ ትርጓሜ ብቻ እንኳን የምርጫውን ውጤት ውድቅ ከማድረግ የተለየ አማራጭ አልነበረንም።” ፊሎሜና ምዊሉ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ‘ውድቅ ይደረግ’ ሲሉ፤ ውሳኔ ካሳለፉት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አንዷ ናቸው።

የ2017ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሕገ መንግስቱና በጽሁፍ በተቀመጡ የአገሪቱ የምርጫ ሕጎች ድንጋጌ መሠረት ያለመካሄዱን ነው ያጤንነው። ግልጽም፣ በማረጋገጫ ሊደገፍ የቻለም አይደለም። በዚህ የሕጉ አግባብ እና በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 83 የሕግ ትርጓሜ ብቻ እንኳን የምርጫውን ውጤት ውድቅ ከማድረግ የተለየ አማራጭ አልነበረንም።” ፊሎሜና ምዊሉ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ‘ውድቅ ይደረግ’ ሲሉ፤ ውሳኔ ካሳለፉት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አንዷ ናቸው።

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የነሃሴውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ለመሠረዝ ያበቃውን ምክኒያት የዘረዘረበትን መግለጫ ዛሬ ይፋ አደረገ።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መግለጫ አያይዞም፤ የኮምፒውተር መረጃ ማከማቻዎች እንዲፈተሹ የሚጠይቀውን የፍርድ ቤት ማዘዣ አልቀበል ብለዋል እና ድምጽ ቆጠራው ሳይጠናቀቅም ውጤቱን ይፋ አድርገዋል ያላቸውን የምርጫ ኮምሽኑን አባላት ነው፤ ተጠያቂ ያደረገው።

ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚያመራው ጎዳና ዛሬ ተዘግቶ ነው፤ የዋለው። ፖሊስ ከቅጥር ጊቢው ውጭ በየፊናቸው የተሰባሰቡትን የገዢውንና የተቃዋሚውን ፓርቲዎች ደጋፊዎች በትኗል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች የነሃሴ አንዱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ውድቅ የተደረገበትን መሠረት ከሰባት ሰዓታት በላይ የሚሆን ወስደው አስረድተዋል።

ፊሎሜና ምዊሉ ሬዝዳንት ዑሁሩ ኬንያታን አሸናፊ ያደረገውን ምርጫ ውጤት ውድቅ ይደረግ ሲሉ ተቀናቃኛቸው ያቀረቡትን ጥሪ ለመደገፍ የወሰኑበትን ምክኒያት ካስረዱት ሦሥት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አንዷ ናቸው።

የኬንያው የምርጫና የድንበር ጉዳዮች ኮምሽን /IEBC/ የኮምፒውተር መረጃ ማከማቻዎቹ እንዲፈተሹ የሚጠይቀውን የፍርድ ቤት ማዘዣ ቸል በማለቱ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የምንሰጥ ዳኞች ሌላ አማራጭ እንዳልነበራቸው ይናገራሉ።

በኬንያ የምርጫ ሥርዓት አፈጻጸም መሠረት፤ የመራጩ ድምጽ የሰፈረባቸው ቅጾች በ291 የተለያዩ የአገሪቱ ምርጫ አካባቢዎች ከሚገኙት 40, 881 የምርጫ ጣቢያዎች ወደ ብሔራዊው የምርጫ ድምጽ ቆጠራ ማዕከል መላክ አለባቸው።

ከእነኚህ የመራጩ ድምጽ የሰፈረባቸው ቅጾች ከሩብ በላይ ያህሉ ተጠናቀው ሳይገቡ የምርጫ ኮምሽኑ አጠቃላዩን የምርጫ ውጤት ይፋ ማድረጉንም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞት ነቅፈዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ዴቪድ ማራጋ የምርጫ አካባቢዎቹን ስብስብ መረጃ ከያዙት ከእነኚህ ቅጾች አብዛኞቹ ያልተሟሉ፤ የሚፈለገው የማረጋገጫ ፊርማ ያላረፈባቸው፤ አለያም የምርጫ ኮምሽኑን አስፈላጊ ገጽታዎች አሟልተው ያልያዙ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የኬንያው ብሔራዊ የምርጫና የድንበር ጉዳዮች ኮምሽን /IEBC/ ከገዢው የጅቢሊ እና የምርጫውን ውጤት ተቃውመው “የውድቅ ይደረግ” ማመልከቻ ካስገቡት የተቃዋሚዎች ሕብረት /NASA/ ጋር ለዛሬ ይዞ የነበረውን ስብሰባ ሁለቱ ወገኖች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለመመዘንና በአዲስ ምርጫ ዙሪያ ለመምከር የመዘጋጃ ጊዜ እንዲያገኙ ለሌላ ጊዜ አስተላልፏል።

ለዳግም ምርጫ የተያዘው ቀጠሮ ለፊታችን ጥቅምት 7 ቢሆንም የተቃዋሚው ወገን የምርጫ ጊዜው እንዲራዘም የሚፈልግ መሆኑን አስታውቋል።

የአገሪቱ ሕገ መንግስት ጠቅላይርድ ቤቱ ብይን በሰጠ ስልሳ ቀናት ውስጥ የዳግም ምርጫ እንዲካሄድ ያዛል። ይህም የመጨረሻውን ቀን ጥቅምት ሃያ አንድ 2010 ያደርገዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኬንያው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔና የምርጫ ኮምሽኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG