የኬንያ መንግሥት የፖሊስ ኃይሉን ወደ ሄይቲ ለመላክ ይዞት የነበረውን ዕቅድ አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባከፈው ሳምንት ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ፣ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
ሄይቲን ያሽመደመዷትን ወሮ በላ ቡድኖች ለመፋለም፣ ኬንያ ዓለም አቀፍ ኃይልን በመምራት እንደምሳተፍ ሩቶ ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ቃል ገብተው ነበር። ተቺዎቻቸው ግን ፕሬዝደንቱ ሕጋዊ ሥልጣን እንደሌላቸው በመናገር ላይ ናቸው።
የቪኦኤ የናይሮቢ ቢሮ ኃላፊ ማሪያማ ዲያሎ የላከችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።
መድረክ / ፎረም