በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ተቃውሞ እንደገና ተጀመረ


ፎቶ ፋይል፦ ናይሮቢ፣ ኬንያ
ፎቶ ፋይል፦ ናይሮቢ፣ ኬንያ

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ እና ባላፈው ዓመት የተደረገው ምርጫ ተጭበርብሯል በሚል በኬንያ ሲደረግ የነበረው ሰልፍ ጋብ ብሎ ቆይቶ የነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ በመዲናዋ ናይሮቢ ቀጥሏል። ፖሊስ በተቃዋሚ የፓርላማ አባላት ላይ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል ተብሏል።

የኬንያው ተቃዋሚ መሪ ፓርቲ የሆነው “አንድ ኬንያ” የፓርላማ አባላት በፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ቢሮ አቅራቢያ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ላይ ሳሉ ፖሊስ የአሰለቃሽ ጋዝ እንደተኮሰባቸው የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የፓርላማ አባላቱ በአገሪቱ የሚታየውን የምግብ፣ ነዳጅ፣ እና የመብራት ዋጋ እጅግ መናርን በተመለከተ ለፕሬዝደንቱ ቢሮ ተቃውሟቸውን ነጽሑፍ ለማስገባት በስፍራው ተገኝተው እንደነበር ሪፖርቱ አመልክቷል።

ባለፈው ወር በተደረጉ ሃይል የተቀላቀለባቸው ተቃውሞዎች ወቅት ሦስት ሰዎች ከሞቱ በኋላ ፖሊስ ሰልፍ እንዳይደረግ ከልክሎ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ በተደረገው ሰልፍ በመዲናዋ ናይሮቢ አንዳንድ ግጭቶች ተስተውለው የነበረ ቢሆንም፣ በአብዛኛው ግን ከተማዋ የተረጋጋች ነበረች ሲል ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG