በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ፖሊስ ናይሮቢ ውስጥ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በቀጥታ ተኮሰ


በሀገር አቀፍ ደረጃ ከታክስ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እና አነጋጋሪ ፀረ-መንግስት ሰልፍ ናይሮቢ፤ ኬንያ
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከታክስ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እና አነጋጋሪ ፀረ-መንግስት ሰልፍ ናይሮቢ፤ ኬንያ

በኬንያ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፀረ-መንግስት ተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት፤ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከስልጣን እንዲወርዱ በሚጠይቁ ሰልፈኞች እና በፖሊስ መሃከል በተቀሰቀሰ ግጭት አንድ ሰው መገደሉን ሮይተርስ አመለከተ።

የሃገሪቱ ሸንጎ አቅርቦት የነበረውን የግብር ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ በመቃወም ከአንድ ወር በፊት የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ፤ ሩቶ ዕቅዱን ውድቅ አድርገው አብዛኛውን የካቢኔያቸውን አባላት ካሰናበቱም በኋላ አላቆመም።

የተቃውሞ አድራጊዎች ሩቶ ስልጣናቸውን እንዲለቁ፣ ሙስና እንዲያበቃ እና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የስርዓት ለውጥ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስካሁን የተካሄዱትን የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ተከትሎ በተቀሰቅሱ ግጭቶች 50 ያህል ሰዎች መገደላቸውን በመንግስት የሚደገፈው የኬንያ የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ ኮሚሽን አስታውቋል።

በተያያዘ ሌላ ዜና ከዋና ከተማይቱ ናይሮቢ ደቡባዊ ዳርቻ ከምትገኘው የኪቲንጌላ ከተማ ድንጋይ በመወረወር እና ጎማ በማቃጠል፤ "ሩቶ ከስልጣ ይውረዱ” የሚል መፈክር ያሰሙ በነበሩ የተቃውሞ አድራጊዎች ላይ ፖሊስ ተኩስ መክፈቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG