በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ፖሊስ ማክሰኞ ወደ ሄይቲ ሊሰማራ ነው ተባለ


ፎቶ ፋይል፦ የታጠቁ የወሮበሎች ቡድን አባላት በፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ፖርት ኦ-ፕሪንስ ውስጥ ሄይቲ፣ እአአ ሚያዚያ 23/2024
ፎቶ ፋይል፦ የታጠቁ የወሮበሎች ቡድን አባላት በፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ፖርት ኦ-ፕሪንስ ውስጥ ሄይቲ፣ እአአ ሚያዚያ 23/2024

ለበርካታ ጊዜያት የዘገየውና የፍርድ ቤትም ጭምር እክል የገጠመው፣ የኬንያ መንግስት ፖሊሶችን ወደ ሄይቲ የማሰማራቱ ዕቅድ፣ በስተመጨረሻ እውን ሊሆን እንደሆነ ዘገባዎች በማመልከት ላይ ናቸው።

መንግስት ወደ ሄይቲ ፖሊሶችን ለማሰማራት የያዘውን ዕቅድ የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሕገ መንግስቱን የሚጻረር ነው ሲል ወስኖ ነበር። ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ አንዱ የሆነው ምክንያት፣ በሁለቱ ሃገራት መካከል የጋራ ስምምነት የለም የሚል ነበር። የኬንያ መንግስት ወዲያውኑ ስምምነት ቢፈጽምም፣ ከሳሾቹ ግን ስምሪቱ እንዳይፈፀም ሌላ ክስ ከፍተዋል።

ወሮበሎች በሚያብጧት ሄይቲ፣ በኬንያ ፖሊሶች የሚመራ ኃይል እንዲሠማራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ባለፈው ዓመት የውሳኔ ሃሳብ አሳልፎ ነበር።

ኬንያ አዲስ የፖሊስ አዛዥ ዛሬ እንደሾመችም ታውቋል።

ከኬንያ በተጨማሪ፤ ቤኒን፣ ባሃማስ፣ ባንግላዴሽ፣ ባርቤዶስ እና ቻድ በሄይቲው ተልዕኮ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።

ሄይቲን ማረጋጋት ሰብዓዊ ግዴታ እንደሆነ የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ሲገልጹ ቆይተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG