በርካቶች ሕይወታቸውን ያጡበት የኬንያ ወጣቶች ተቃውሞ አያይዝን በተመለከተ የተሰነዘረውን ትችት ተከትሎ የፖሊስ አዛዡ ዛሬ ዓርብ ሥራቸውን ለቀዋል።
የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የጃፈት ኩሜን የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ እንደተቀበሉ ከቢሯቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል።
የፖሊስ አዛዡ መልቀቅ ዜና የመጣው ፕሬዝደንት ሩቶ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ካቢኔያቸውን በበተኑ ማግስት ነው።
አዲሱ ትውልድ በማኅበራዊ ሚዲያ በመደራጀት የሚደርገው ተቃውሞ የሩቶን የሁለት ዓመታት ሥልጣን ክፉኛ የተፈታተነ ሲሆን፣ የታክስ ጭመራ ዕቅዳቸው እንዲተዉ እና ካቢኔያቸውን እንዲበትኑ አስገድዷል።
ሆኖም ግን ወጣት ተቃዋሚዎቹ ፕሬዝደንት ሩቶ ሥልጣናቸውን ካለቀቁ የመንገድ ላይ ተቃውሟቸውን እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።
በተቃውሞዎቹ እሰከ አሁን 39 ሰዎች እንደሞቱ የመብት ተሟጋች ቡድኖች ያስታውቃሉ።
መድረክ / ፎረም