በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች


ኬንያ ፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች

ኬንያ ፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች፣ ህጉ ከትላንት ጀምሮ በሥራ ላይ መዋል የጀመረ ሲሆን፣ ፕላስቲክ ፌስታል ማምረትንና መጠቀም ተከልክሏል።

በዚህም ህጉን ተላልፎ የተገኘ ማንኛዉም ሰዉ 38,000 የአሜርካን ዶላር ቅጣት ወይም የ4 ዓመት እሥራት ይበየንበታል። ህጉ የአከባቢ አየር ብክለትን ለመቆጣጠር የወጣ ሲሆን፣ በፕላስቲክ ፌስታል ፋብሪካ ዉስጥ የሚሰሩ 80,000 የሃገሪቱ ዜጎችን ሥራቸውን አሳጥቷቸዋል።

ለዓመታት በሃገሪቱ ህግ መወሰኛ ፍ/ቤት ተፈጻሚነቱ ሲጓተት የነበረዉ በኬንያ የፕላስቲክ ፌስታል መጠቀምን የሚከለክለዉ ህግ ፀድቆ በሥራ ላይ ውሏል። በዚህም ህጉ እንደ ተደነገገዉ ከትላንት ጀምሮ የፕላስቲክ ፌስታልን የሚያመርት፣ የሚሸጥ ወይም ይዞ የተገኘ እስከ 38,000 የአሜርካን ዶላር ወይም የ4 ዓመት እሥራት እንዲበየንበት ታዉጇል።

የህጉ ተፈጻሚነት አሁን የፕላስቲክ ፌስታል አምራቾችን እና አስመጪዎችን ሙሉ በሙሉ ማገድ ላይ ያተኮረ ሲሆን በሂደትም ወደ ግለሰብ ወርዶ ተፈጻሚ እንደሚሆን የኬንያ የአካባቢ አየር ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።

እርምጃዉ የአካባቢ አየር መበከልን ለመቀነስ የተወሰደ ቢሆንም የተለያዩ የፕላስቲክ ፌስታል ማምረቻ ፋብሪካ ዉስጥ ተቀጥረዉ ይሠሩ የነበሩ ከ80 ሺህ በላይ የሃገሪቱ ዜጎች ሥራቸዉን እንዲያጡ ምክንያት ሆኖአል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኬንያ ፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:54 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG