በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዳዳብና እና ካኩማ የስደተኛ ካምፖች ሊዘጉ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ዳዳብ ካምፕ
ፎቶ ፋይል፦ ዳዳብ ካምፕ

ኬኒያ በብዙ መቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የአጎራባች ሶማሊያ ስደተኞች የተጠለሉባቸውን ግዙፎቹ ዳዳብ እና ካኩማ የስደተኛ ካምፖች እንዲዘጉ በዛሬው ዕለት ትዕዛዝ ሰጠች። ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዕቅዱን እንዲያቀርብ የሁለት ሳምንት ጊዜ ተሰጥቶታል ሲል የሀገር ደህንነት ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በሰሜን ኬንያ የሚገኙት ዳዳብና ካኩማ የስደተኛ ካምፖች ከ410 ሺህ በላይ ስደተኞች አስጠልሏል፤ ቁጥራቸው ጥቂት ደቡብ ሱዳናውያን ስድተኞችም እንደሚገኙ ተገልጿል።

የኬንያ ባለሥልጣናት እአአ በ2016 የብሄራዊ ጸጥታ ስጋት አለን የሚል ምክንያት ሰጥተው ከካኩማ ይበልጥ ለሶማሊያ ድንበር ቀረብ የሚለውን ዳዳብ ካምፕን ለመዝጋት እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር።

በአሁኑ መመሪያ ግን የኬንያ አገር ወስጥ ደህንነት ሚኒስትሩ ፍሬድ ማቲያንጊ ለዩኤንኤችሲአር ሁለቱንም ካምፖች የሚዘጋበትን ዕቅድ እንዲያቀርብ የሁለት ሳምንት ጊዜ ሰጥተነዋል፣ ያለቀ ጉዳይ ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ዩኤንኤችሲአር በበኩሉ ኬንያ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ማግኘታቸውን እንድታረጋግጥ ጠይቀናል፤ በጉዳዩ ላይ መንግሥቱን ማነጋገራችንን እንቀጥላለን ብሏል።

XS
SM
MD
LG