በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ፀረ-መንግሥት የተቃውሞ ሰልፍ አንድ ሰው በጥይት ተመታ


በኬንያ ፀረ-መንግሥት የተቃውሞ ሰልፍ አንድ ሰው በጥይት ተመታ
በኬንያ ፀረ-መንግሥት የተቃውሞ ሰልፍ አንድ ሰው በጥይት ተመታ

በኬንያ መዲና ናይሮቢ የኑሮ ውድነት እጅግ በመናሩ ምክንያት ተማረው ሰልፍ በወጡ ኬንያውያን ላይ ፖሊስ አሰለቃሽ ጭስ ውርውሯል። አንድ ሰልፈኛ በጥይት መመታቱ ሲታወቅ፣ ያለበትን ሁኔታ ወዲያውኑ ማወቅ አልተቻለም።

ባለፈው ነሃሴ በምርጫ ሥልጣን በተቆጣጠሩት ዊሊያም ሩቶ አስተዳደራቸውን በተመለከተና እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድንነት በመቃወም የተቃዋሚ መሪው ራይላ ኦዲንጋ ሰልፉን መጥራታቸው ታውቋል።

ተቃዋሚው ኦዲንጋ ፕሬዚዳንት ሩቶ ምርጫውን አጭበርብረው ሥልጣን ይዘዋል ሲሉ ይከሳሉ። የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመጭበርበሩ በቂ ማስረጃ የለም ሲል ውጤቱን አጽድቋል።

ሰልፈኞቹ እየናረ ስለመጣው የኑሮ ውድነት፣ ምርጫ ስለመጭበበሩና በፕሬዚዳንት ሩቶ መንግሥት ውስጥ አለ ስለሚሉት ሙስና ተናግረዋል።

ፖሊስ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጭስና በውሃ እንደበተነና ቢያንስ አንድ ሰው በጥይት እንደተመታ የቪኦኤው ሞሃመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ከላከው ዘገባ ማወቅ ተችሏል።

ኦዲንጋ ለደጋፊዎቻቸው ባደርጉት ጥሪ የተቃውሞ ሰልፉ በየሳምንቱ ሰኞ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG