በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመካከለኛው ምስራቅ የተበደሉ የኬንያ ተመላሽ ሠራተኞች እየተቋቋሙ ነው


በመካከለኛው ምስራቅ የተበደሉ የኬንያ ተመላሽ ሠራተኞች እየተቋቋሙ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00

በመካከለኛው ምስራቅ የተበደሉ የኬንያ ተመላሽ ሠራተኞች እየተቋቋሙ ነው

ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሄዱ የኬንያ ሠራተኞች፣ በአሠሪዎቻቸው ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የእርዳታ ተቋማት ደግሞ፣ ስደተኞቹ ሠራተኞች በኬንያ ተመልሰው ህይወታቸውን የሚያደራጁበትን እድል እየሰጧቸው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

በደል የተፈጸመባቸውና ለጉልበት ሥራ የተዳረጉ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች፣ ዛሬ የመቋቋሚያና የማረፊያ እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶችን እገዛ ማግኘት ጀምረዋል፡፡

በኬንያ መዲና ናይሮቢ ወጣ ብሎ የሚገኘው የፌይት ሙሩንጋ መደብር ለንግድ አገልግሎት ተከፍቷል፡፡ ቤተሰቧን ለመመገብ የጀመረችው ሲሆን አሁን ስድስት ወር ሆኖታል፡፡

ኬንያ ውስጥ ሥራ ማግኝት ለተሳናቸው ብዙዎቹ ዜጎች የተሻለ እንጀራ ፍለጋ መዳረሻ ወደ ሆነችው ሳኡዲ አረብያ እኤአ በ2019 ኬንያን ትታ ሄደች፡፡

ወደ ሳኡዲ አረብያ ስትሄድ ያገኘችው የጠበቅችውን አልነበረም፡፡ ቃል የተገባላትና ስትሄድ የጠበቃት እጅግ የተለያዩ ነበሩ፡፡

እንዲህ ትገልጸዋለች

“አለቃዬ መጣና ወደ አገራቸው መሄድ እስከተስማማው ድረስ የተባልኩትን ምንም ነገር ሁሉ ማድረግ ይኖርብኛል፡፡ ምንም ዓይነት ቅሬታ የማቅረብ መብት እንደሌለኝ ነገረኝ፡፡ እኔን ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ከፍለዋል፡፡ ስለዚህ እኔ ንብረታቸው ነኝ ማለት ነው፡፡”

በሳኡዲ አረብያ በቆየችባቸው ሁለት የሥራ አመታት፣ ሙሩንጋ በአሰሪዎቿ የመንፈስና የአካል ጥቃት ደርሶባታል፡፡ በጎ አድራጊዎች መጥተው ወደ ኬንያ እስክትመለስ ድረስ ጥቃቱ አልተለያትም፡፡

ወደ አገሯ ስትመለስ ከኻራት ኬንያ እርዳታ አግኘታለች፡፡ኻራት ኬንያ የሰዎችን ህገወጥ ዝውውርን የሚታገልና እንደ ፌት ያሉ ሰዎችን የሚረዳ ነው፡፡

ድርጅቱ እስከተቋቋመበት እኤአ 2010 ድረስ፣ በግዴታ ሥራ ተሰማርተው፣ በደረሰባቸው ጥቃት ሰግተው፣ ወደ አገራቸው የተመለሱ ወደ 700 የሚደርሱ ሰዎችን ረድቷል፡፡

ሜርሲ አቲዬኖ፣ የድርጅቱ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ እርዳታ በሚፈለጉበት ወቅት፣ ካገኘናቸው ሴቶች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆኑት የተለያዩ ስቃዮችና ግፎች የደረሱባቸው ናቸው ይላሉ፡፡

ይህኑን ሲገልጹም እንዲህ ብለዋል

“ሠራተኞቹ ወደኛ ሲመጡ የተጨነቁ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ በደል የደረሰባቸው ይመስላል፡፡ ቀጥለው ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም፡፡ ወይም ከየት መጀመር እንዳለባቸው የሚያውቁ አይደሉም፡፡ መኖሪያ ቤት የላቸውም ወደ አገራቸው መመለስ አይፈልጉም፣ ሁሉም ሰው ወደ ውጭ አገር መሄዳቸውን ነው የሚያውቀው ፡፡ አንድ ነገር ይዘው ይመለሳሉ ብሎ ነው የሚጠብቀው፡፡”

ድርጅቱ ከጥቃቱ የተረፉትን ወይም ለግዳጅ ስራ የተዳረጉትንም ሆነ ከሥራ ጋር በተያያዘ ጥቃት የደረሰባቸውን በመቀበል ህይወታቸውን መልሰው እንዲያቋቁሙ ይረዳሉ፡፡ በምክር ሥልጠና በመስጠት እና ራሳቸውን ችለው የሚኖሩበትን መንገድ በማመቻቸት ይረዷቸዋል፡፡

አቲዬኖ እንዲህ ይላሉ

“ጉዳያቸውን የሚከታተሉትና፣ ተበዳዮቹ ሠራተኞቹ አንድ ላይ ሆነው፣ ለተሀድሶው አብረው የሚሠሩበት ይህ ሂደት፣ በጣም አሳታፊ ሂደት ነው፡፡ ስለዚህ የተበደሉት ሠራተኞች የሚጠየቁትን ሁሉ ነገር ላለመስራት፣ እምቢ የሚሉበት ድምጽ ይኖራቸዋል፡፡ ምክንያቱም የምንሰጠው አገልግሎት በየግል የሚሰጥና ተበዳዮችን ያማከለ ነው፡፡”

በኬንያ ለሠራተኞች መብት የሚታገል ፣ የአገር ውስጥ የሆቴል፣ የትምህርት ተቋማት፣ ሆስፒታሎችና ተባባሪ ሠራተኞች ህብረት ማህበር፣ አለ፡፡ ይህ ማህበር “በኬንያ የሚገኘው የሥራ አጥነት ቁጥር 10 ከመቶ በላይ በመሆን ከፍ ብሎ እስከ ቀጠለ ድረስ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚሄዱ የስደት ሠራተኞች የሚቀጥል ነው ይላል፡፡”

አልበርት ነጅሩ የማህበሩ ዋና ጸሀፊ ሲሆኑ፣ ምንም ሥልጠና ፣ምንም መረጃ ሳይኖራቸው፣ ወደ ውጭ ለሚሄዱ ሠራተኞች የሚከተለውን ምክር ይሰጣሉ

“ተቢውን መረጃ ፈልጉ፣ በስፋት አማክሩ፣ ትክክለኛውን ነገር ከማግኘታችሁ በፊት ጨለማ ወደ ሆነው ነገር አትመልከቱ፡፡”

የኻራት ኬንያ አመራር እንደ ፌይት ያሉ ጉዳዮች ሲገጥሙት ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡ ለአሁኑ ግን፣ ፌትም ለተደረገላት ነገርና በውጭ አገር ከተፈጸመባት ግፍና በደል በመዳን፣ ህይወትዋን እንደገና ለመጀመር ለተሰጣት እድል የምታመሰግን መሆኑን ተናግራለች፡፡

XS
SM
MD
LG