በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕግ ባለሞያዎች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በናይሮቢ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ


በናይሮቢ ከተማ የተካሄደው የተቃዉሞ ሰልፍ
በናይሮቢ ከተማ የተካሄደው የተቃዉሞ ሰልፍ

የኬንያ የሕግ ባለሞያዎች ማህበር ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጋር በመሆን በናይሮቢ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ። በተቃዉሞዉ ሰልፍ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የህግ ባለሞያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለሰቦች የተሳተፉበት ሲሆን መንግስት በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለዉን ግድያ ለማስቆም የበኩሉን መወጣት አልቻለም ሲሉ ተችተዋል።

ከሳምንት በፊት ዊሊ ኪማኒ የተባለ ጠበቃ የፖሊስ እጅ አለበት የተባለዉን ወንጀል በማጣራት ላይ እያለ ባልታወቀ ሁኔታ ከታክሲ ሾፌራቸው ጋር ተገድሎ በዶንያ ተጥሎ ተገኝተዋል። የጠበቃዉ ደምበኛ እስካሁን የት እንደገባ የሚታወቅ ነገር የለም። በተቃዉሞዉ ሰልፍ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንተርናሽናል ፎር ጃስትስ ሚሽን በኬንያ ኃላፊ አቶ ጄምስ ኪሮጊ 'የግድያ ወንጀል ከ100 የኬንያ ወንዶች በአንዱ ላይ የሚደርስ ነው'በማለት መንግስት በቂ እርምጃ ያልወሰደበት ወንጀል ነዉ ብሏል።

በናይሮቢ ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ
በናይሮቢ ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ

ይህ በእንዲህ እያለ ግድያዉን በማስመልከት የኬንያ ፖሊስ ሁለት ተጠርጣሪ ፖሊሶችን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ፖሊስ መረጃ እስከሚያሰባስብ ድረስ ፍርድ ቤት ለተያዙት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የሁለት ሳምንት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የሕግ ባለሞያዎች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በናይሮቢ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG