አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራሉ ፍርድ ቤት ዳኛ ዕገዳው ላይ ማዕቀብ ቢጥሉም፣ ወደ አሜሪካ ሊጓዙ የተዘጋጁ የሶማልያና የሱዳን ስደተኞች ግን ወደ ካኩማ እና ዳዳብ መጠለያ ጣቢያዎች እንዲመለሱ ተደርገዋል።
ሌሎች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመምጣት በዝግጅት ላይ ያሉ ስደተኞችም በነገሩ እየተጨነቁ ናቸው፤ ይሁንና ተስፋ ባለመቁረጥ፣ ዕገዳው ይነሳል በሚል እምነት ላይ መሆናቸው ታውቋል።
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዞ ዕገዳ የወደፊት የጥገኝነት ማረፊያቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከሆነ ካኩማ እና ዳዳብ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ባሉ ስደተኞች ላይ አያሌ ጭንቀትና ውዥንብር መፍጠሩ እየተሰማ ነው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ